Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 36:5
32 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።


አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?


በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።


ጌታ ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።


እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ስለ አሞን ልጆች፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ታዲያ ሚልኮምስ ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ለምን ተቀመጠ?


ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና


ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆች እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ የሕዝቦችን ስድብ ተሸከማችሁአልና፤


በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት ተናግሬአለሁ፦ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ መናወጥ ይሆናል፤


ንዴቴ ያልፋል፥ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ እንዲያርፍ አደርጋለሁ፥ እጽናናለሁም፥ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ በፈጸምሁ ጊዜ እኔ ጌታ በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።


ነገር ግን በወንድምህ የመከራ ቀን ልትደሰት፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች መጥፋት ደስ ሊልህ፥ በጭንቀታቸውም ቀን በትዕቢት ልትናገር አይገባም ነበር።


ጠላቴ ሆይ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ብወድቅ እነሣለሁና፤ በጨለማ ብቀመጥ ጌታ ብርሃኔ ነውና።


ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።


ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፥ ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


ያደረገውን ነገር ሁሉ ሰምተው፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ፥ ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።


ጌታ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos