ሕዝቅኤል 28:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፤ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርሷም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኀጢአትህና በተጭበረበረው ንግድህ ብዛት፣ መቅደስህን አረከስህ። ስለዚህ እሳት ከአንተ እንዲወጣ አደረግሁ፤ እርሱም በላህ፤ በሚመለከቱህ ሁሉ ፊት፣ በምድር ላይ ዐመድ አደረግሁህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበደልህ ብዛት፥ በንግድህም ኀጢአት መቅደስህን አረከስህ፤ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ፤ እርስዋም በልታሃለች፤ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፥ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ። |
በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።
የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።
ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”
የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”