Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነሆ፥ ጌታ ሀብቷን ይገፍፋታል፥ ወደ ባሕርም ውስጥ ያሰምጠዋል፤ እርሷም በእሳት ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤ እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን የሰበሰበችውን ሁሉ እግዚአብሔር ይወስድባታል፤ ሀብትዋን ወደ ባሕር ይጥለዋል፤ ከተማይቱም በእሳት ተቃጥላ ዐመድ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፣ እርስዋም በእሳት ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነሆ፥ ጌታ ይገፍፋታል፥ በባሕርም ላይ ያለውን ብርታትዋን ይመታል፥ እርስዋም በእሳት ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 9:4
14 Referencias Cruzadas  

በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፤ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርሷም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።


በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!


በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የእርሷንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”


ጌታ ተናግሮአልና ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን በይሁዳ ልጆች እጅ እሸጣለሁ፥ እነርሱም ለሩቆቹ ሕዝብ ለሳባ ሰዎች ይሸጡአችኋል።


በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።


ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤ በባሕር ልብ ተገድለው በሞቱበት ሞት ትሞታለህ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


በክፋት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።


እጁን በባሕር ላይ ዘረግቶ መንግሥታትንም አናውጧል፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ ጌታ አዟል።


አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ በሥጋት ትታመማለች፤ እንዲሁም አቃሮን፥ ተስፋዋ ይመነምናል። ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚኖር አይገኝም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios