ሕዝቅኤል 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ ዙፋን ላይ፣ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ። ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር መካከል ተቀምጫለሁ ብለሃል፥ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። Ver Capítulo |