ሕዝቅኤል 26:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ዘውዳቸውን ከራሳቸው ያወርዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ፤ በመሬትም ላይ ተቀምጠው ይደነግጣሉ፤ ሞታቸውንም ይፈራሉ፤ ስለ አንቺም ያለቅሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፥ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፥ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ በአንቺም ይደነቃሉ። |
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።”
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩን ስለ እርሱ ሸፈንሁት፥ ፈሳሾቹን ገታሁ፥ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።
ብዙም ሕዝቦች አንተን አይተው እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ይንቀጠቀጣሉ፤ በወደቅህበትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።
ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
አሁን በቅርብ መዓቴን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እፈጽማለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።