Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 31:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩን ስለ እርሱ ሸፈንሁት፥ ፈሳሾቹን ገታሁ፥ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ መቃብር በወረደበት ቀን ጥልቅ ምንጮችን ስለ እርሱ በሐዘን ሸፈንኋቸው፤ ወንዞቹን ገታሁ፤ ታላላቅ ፈሳሾችም ተቋረጡ። በርሱም ምክንያት ሊባኖስን ጨለማ አለበስሁ፤ የደን ዛፎችም ሁሉ ደረቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወ​ረ​ደ​በት ቀን ልቅ​ሶን አስ​ለ​ቀ​ስሁ፤ ቀላ​ዩ​ንም ስለ እርሱ ሸፈ​ን​ሁት፤ ፈሳ​ሾ​ች​ንም ከለ​ከ​ልሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም ውኆች ተከ​ለ​ከሉ፤ ሊባ​ኖ​ስ​ንም ስለ እርሱ አሳ​ዘ​ን​ሁት። የዱ​ርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት ፈሳሾቹንም ከለከልሁ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 31:15
8 Referencias Cruzadas  

እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


አሁን በውድቀትሽ ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕር ያሉ ደሴቶችም ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።


በማጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶቻቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም።


በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ዱሮው ዘመንና እንደ ቀደሙት ዓመታት ጌታን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos