Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብ መሪዎች መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤ የሞዓብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤ የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የኤዶም መሪዎች ተስፋ ቈረጡ፤ የሞአብም ኀያላን ተንቀጠቀጡ፤ የከነዓንም ሕዝብ ወኔ ከዳቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞአብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 15:15
24 Referencias Cruzadas  

እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነግሥታት ሁሉ፥ ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩት ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ከዚያ ወዲያ ሐሞተ ቢስ ሆኑ።


ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል።


ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ “ጌታ ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ ከእናንተም የተነሣ በፍርሃት መዋጣችንን፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ በፍርሃት እንደ ቀለጡ አወቅሁ።


ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።


የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው፥ በስፍራቸውም፥ በስማቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥


የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።


ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ፤ ሃብቷ ማለቂያ የለውምና፥ የከበረው የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቆጠርምና።


እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለ ግብጽ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ጌታ በፈጣን ደመና እየበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።


ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።


እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።


አባትህ ታላቅ ጦረኛ፥ አብረውት ያሉትም ጀግኖች መሆናቸውን እስራኤል ሁሉ ስለሚያውቅ፥ ልቡ እንደ አንበሳ ልብ የሚደፍረው እንኳ በፍርሀት ይርዳል።


በብንያም ግዛት በጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ሠራዊት በየአቅጣጫው መበታተኑን አዩ።


ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ።


ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።”


“ከዚያም አለቆቹ፥ ‘የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ’ በማለት ጨምረው ይናገሩ።


የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፥ የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የቴማን አለቃ፥ ኦማር አለቃ፥ ስፎ አለቃ፥ ቄናዝ አለቃ፥


እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።


ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ ቀለጡም፤ ለማረፍም እንደማይችል ባሕር በፍርሃት ተናወጡ።


ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው።


ቆመ፥ ምድርንም አንቀጠቀጣት፥ ተመለከተ፥ ሕዝቦችንም አስደነገጠ፥ የዘለዓለም ተራሮች ተናጉ፥ የጥንት ኮረብቶች አጎነበሱ፥ የጥንት መንገዶች የእርሱ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios