እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
ሕዝቅኤል 24:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርሷ ላልወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቁራጭ ቁራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ለዛገችው ብረት ድስት ዝገቷም ለማይለቅ፣ ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት! መለያ ዕጣ ሳትጥል አንድ በአንድ አውጥተህ ባዶ አድርገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ ወዮላት! ከዝገቱ እንዳልጠራና ከቶም እንደማይጠራ ብረት ድስት ሆናለች፤ በውስጥዋ ያለውን ቊራጭ ሥጋ ሳትመርጥ አንድ በአንድ አውጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገቷ ላለባት፥ ዝገቷም ከእርስዋ ላልወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቍራጭ ቍራጩን አውጣ፤ ዕጣ አልወደቀባትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርስዋ ላልወጣ ምንቸት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቍራጭ ቍራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም። |
እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ ከተማ ሆይ!ጊዜዋ ደርሶአል፥ እንድትረክስም በራስዋ ላይ ጣዖታትን የምታደርግ፤
በዳር ቆመህ በተመለከትክበት ቀን፥ አሕዛብ ሀብቱን በማረኩበት፥ ባእዳን በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተም እንደ እነርሱ ነበርህ።
እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።
በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።