Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኩሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ አትፈርድባትምን? ደም በምታፈስሰው በዚህች ከተማ ላይ አትፈርድባትምን? ጸያፍ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! በነፍሰ ገዳዮች የተሞላችውን ከተማ ልትፈርድባት ተዘጋጅተሃልን? እንግዲያውስ የፈጸመቻቸውን አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ገልጠህ አሳያት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ደም በም​ታ​ፈ​ስስ ከተማ ላይ ትፈ​ር​ዳ​ለ​ህን? ርኵ​ሰ​ቷን ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 22:2
22 Referencias Cruzadas  

ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ማታለልና ዘረፋ ሞልቶባታል፤ ንጥቂያ ከእርሷ አይርቅም።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮላት! እኔ ደግሞ ማገዶውን ብዙ አደርገዋለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርሷ ላልወጣ ድስት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቁራጭ ቁራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም።


ትፈርድባቸዋለህን? የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርድባቸዋለህን? የአባቶቻቸውን ርኩሰት አስታውቃቸው፤


በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጽ።


ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም።”


ሕዝቡም ሁሉ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” ብለው መለሱ።


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።


ስለዚህም ይህ ትውልድ ተጠያቂ የሚሆነው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በፈሰሰው በነቢያት ሁሉ ደም፥


በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።


እንዲሁም ሲምሱ አልያዝሻቸውም ነገር ግን በልብሶችሽ ላይ የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብትፈጽሚም እንኳ


ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ ሰይፋችሁ እንደሚሰባብር አንበሳ ነብዮቻችሁን በልቶአል።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


በዚህች ከተማ ውስጥ የገደላችኋቸውን አብዝታችኋል፥ ጎዳናዎችዋንም በተገደሉት ሞልታችኋል።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ ከተማ ሆይ!ጊዜዋ ደርሶአል፥ እንድትረክስም በራስዋ ላይ ጣዖታትን የምታደርግ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios