ሕዝቅኤል 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር ወዳዘጋጀሁላችሁ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር አወጣቸው ዘንድ ማልሁላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን፣ ከግብጽ አውጥቻቸው ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወዳዘጋጀሁላቸውም ምድር እንደማስገባቸው ማልሁላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ቀን ከግብፅ ምድር ወዳዘጋጀሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ ከምድር ሁሉ ወደምትበልጥ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጄን አነሣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር ወዳዘጋጀሁላችሁ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር አወጣቸው ዘንድ ማልሁላቸው፥ |
ጌታም ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኤዊያውያን፥ ወደ ኢያቡሳውያንም ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር ባገባህ ጊዜ ይህችን አገልግሎት በዚህ ወር ታገለግላለህ።
ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’
ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ እሰጣታለሁ ብዬ እጄን ወደ አነሳሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ እርሷንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’”
ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት።
እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።
እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፥ ለያዕቆብ ቤት ዘር ማልሁላቸው፥ በግብጽም ምድር ራሴን ገለጥሁላቸው፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ ብዬ ማልሁላቸው።
ነገር ግን እኔ እንዲህ አልኋችሁ፦ ‘ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እንድትወርሱአትም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ።’ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
በማያውቋቸው በባዕዳን አሕዛብ መካከል በዐውሎ ነፋስ በተንኳቸው። ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚዘዋወርባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፤ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።
ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’
የአባቶችህ አምላክ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ ማርና ወተት ወደምታፈሰው ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፥ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው።
ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።
ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።