ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
ሕዝቅኤል 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ የሰንፔር ዙፋን የሚመስል ነገር ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የሰው መልክ የሚመስል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠፈሩም በላይ ሰንፔር ተብሎ ከሚጠራ ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር ተዘርግቶ ነበር፤ ሰው የሚመስልም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራሳቸውም በላይ ከአለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሳቸውም በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፥ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ። |
ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።
እርሱ የጌታን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይጐናጸፋል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ መግባባት ይኖራል።
የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።
ከዚያም አየሁ፤ እነሆም ነጭ ደመና በደመናውም ላይ የሰው ልጅን የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።
በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።