Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 54:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አንቺ የተሸገርሽ በአውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ የተሠቃየሽ፥ በዐውሎ ነፋስም የተዋከብሽና ያልተጽናናሽ የኢየሩሳሌም ከተማ! እኔ በከበረ ድንጋይ እሠራሻለሁ፤ መሠረትሽንም የምጥለው በሰንፔር ድንጋይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አንቺ የተ​ቸ​ገ​ርሽ የተ​ና​ወ​ጥሽ ያል​ተ​ጽ​ና​ና​ሽም፥ እነሆ፥ ድን​ጋ​ዮ​ች​ሽን የሚ​ያ​በሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ት​ሽ​ንም የሰ​ን​ፔር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አንቺ የተሸገርሽ በዓውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 54:11
43 Referencias Cruzadas  

‘ማንም የማይሻት ጽዮን!’ ‘የተጣለች’ ብለው ጠርተውሻልና እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቁስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል ጌታ።


እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።


በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”


እኔም አየሁ፥ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ፥ ዙፋን የሚመስል ነገር ታየ።


ጌታ እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፥ ይላል አምላክሽ።


ስለዚህ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ አንቺ ችግረኛ፥ ይህን ስሚ፤


ጽዮን ግን፦ “ጌታ ትቶኛል፥ እርሱ ረስቶኛል” አለች።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ “የሚያምን አያፍርም።”


ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መልስ ይሰጣል? “ጌታ ጽዮንን መሥርቷል፥ ከሕዝቡም ችግረኞች በእርሷ ውስጥ መጠጊያን ያገኛሉ።”


ጌታ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።


በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


እነሆ ማዕበሉ ጀልባይቱን እስኪሸፍናት ድረስ በባሕሩ ላይ ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር።


ከራሳቸው በላይ ካለው ሰማይ በላይ ዙፋን የሚመስል ነበረ፥ እርሱም የሰንፔር ድንጋይ ይመስል ነበር፥ ዙፋን በሚመስለው፥ በላዩ ላይም ሰው የሚመስል ነበረ።


ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።


ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።


እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ ያለበት የወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው።


በዚህ ዓይነት ሠራተኞቹ በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆኑ ታላላቅ ድንጋዮችን ፈለጡ።


በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።


የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማያት የጠራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።


ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


የጌታም መልአክ በእሳት ነበልባል በቁጥቋጦው መካከል ታየው፤ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቁጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።


ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።


ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።


በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።


ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ።


የግንብሽንም ጉልላት በቀይ ዕንቁ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቁ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።


ቅጥርሽ የሚሠራበት ቀን፥ በዚያ ቀን ድንበርሽ ይስፋፋል።


እርሱም ከውስጥና ከውጪ በኩል ያሉትን ክፍሎች ወለል እንኳ በወርቅ ለበጣቸው።


ቤቱንም በዕንቁ አስጌጠው፤ ወርቁም የፈርዋይም ወርቅ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios