Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 45:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው። በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አሕ​ዛብ ደነ​ገጡ ነገ​ሥ​ታ​ትም ተመ​ለሱ፤ ልዑል ቃሉን ሰጠ፥ ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 45:6
18 Referencias Cruzadas  

ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፥ አንተም ከዘለዓለም ጅምሮ አለህ።


በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።


መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ለዘለዓለምም ጽኑ ፍቅሬን ለእርሱ እጠብቃለሁ፥ ኪዳኔም በእርሱ ዘንድ የታመነ ነው።


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።


እግዚአብሔርም ከግብጽ አውጥቶታል፤ ጉልበቱ አንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል።


ከተገደሉት ደም፥ ከተማረኩትም ደም፥ ከጠላት አለቆችም ራስ፥ ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፥ ሰይፌም ሥጋ ይቆራርጣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios