ሕዝቅኤል 1:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ወገቡ ከሚመስለው ወደ ላይ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል፥ ቤቱም በእሳት የተከበበ የሚመስል አየሁ፥ ወገቡ ከሚመስለው ወደ ታች ደግሞ በዙሪያው ብርሃን ያለው እሳት የሚመስል አየሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ በእሳት መካከል እንዳለ የጋለ ብረት፣ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል እንደ ነበር አየሁ፤ ደማቅ ብርሃንም በዙሪያው ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ወገቡ ከሚመስለው ክፍል በላይ እሳት ውስጥ ገብቶ የጋለ ብረት የሚመስል ነገር ከወገቡም በታች እሳት የሚመስል ነገር አየሁ፤ የሚያንጸባርቅ ብርሃንም ዙሪያውን ገብቶበታል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ አምሳያ አየሁ፤ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አምሳያ አየሁ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ አየሁ፥ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት ምስያ አየሁ፥ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ። Ver Capítulo |