ዘፀአት 9:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳትለቅቃቸው አሁንም በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስካሁንም በሕዝቤ ላይ እንደ ተነሣህ ነው፤ ይሄዱም ዘንድ አትለቅቃቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ እስከ አሁንም በሕዝቤ ላይ ታብየሃል፤ እንዲሄዱም አልፈቀድክላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን እንዳትለቃቸው ገና በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳትለቅቃቸው ገና በሕዝቤ ላይ ራስህን ከፍ ከፍ ታደርጋለህን? |
እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።
መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?