ዘፀአት 22:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበለቲቱንና ድሀ አደጉን አታስጨንቁአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተ በግብጽ መጻተኛ ነበራችሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ መጻተኛውን በመጨቈን አታጒላሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና ስደተኛውን አትበድሉት፤ ግፍም አታድርጉበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና ስደተኛውን አትበድለው፥ ግፍም አታድርግበት። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥
እናንተ በግብጽ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገሩ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፥ እርሱንም እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
በዚያን ጊዜ ፈራጆቻችሁን አዘዝኋቸው። አልኋቸውም፦ ‘የወንድሞቻችሁን ነገር ስሙ፥ በሰውና በወንድሙ ከእርሱም ጋር ባለው መጻተኛ መካከል በጽድቅ ፍረዱ።