የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፦ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፥ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፥ ጌታም ረዳው፥ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።
ዘፀአት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን በቀረበ ጊዜ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ እነሆ፣ ግብጻውያን ይከታተሏቸው ነበር፤ እነርሱም በታላቅ ፍርሀት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ንጉሡና ሠራዊቱ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል መምጣታቸውን አይተው እጅግ ፈሩ፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዐይናቸውን አነሡ፤ እነሆም፥ ግብፃውያን ሲከተሉአቸው አዩ፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዐይናቸውን አነሡ፤ እነሆም ግብፃውያን በኋላቸው ገሥግሠው ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ። |
የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፦ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፥ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፥ ጌታም ረዳው፥ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።
እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና።
እርሱም ወደ ጌታ ጮኸ፤ ጌታም ዛፍ አሳየው፥ በውኃውም ላይ ጣለው፥ ውኃውም ጣፋጭ ሆነ። ጌታም በዚያ ሥርዓትንና ፍርድን አደረገላቸው፥ በዚያም ፈተናቸው፤
ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።
“ጌታ አምላክህን በምድረ በዳ እንዴት እንዳስቆጣኸው፥ ከግብጽ ምድር ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በጌታ ላይ እንዳመፃችሁ አስታውስ፥ አትርሳም።
አባቶቻችሁንም ከግብጽ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፤ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።
ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።