Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም በእናንተና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረገ። ባሕሩን በላያቸው አመጣ፤ አሰጠማቸውም። በግብጻውያን ላይ ያደረግሁትንም ራሳችሁ በዐይናችሁ አያችሁ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ኖራችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጮ​ሃ​ችሁ ጊዜ በእ​ና​ን​ተና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን መካ​ከል ደመ​ና​ንና ጭጋ​ግን አደ​ረ​ግሁ፤ ባሕ​ሩ​ንም መለ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ አሰ​ጠ​ማ​ቸ​ውም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በግ​ብፅ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን አዩ፤ በም​ድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወደ እግዚአብሔርም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፥ ዓይኖቻችሁም በግብፅ ያደረግሁትን አዩ፥ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 24:7
14 Referencias Cruzadas  

ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ፤ ደመናና ጨለማ ነበረ፥ ሌሊቱን አበራ፤ ሌሊቱን ሙሉ ማንም አልቀረበም።


ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ።


እስራኤልም ጌታ በግብጽ ላይ ያደረጋትን ታላቅ ኃይል አየ፥ ሕዝቡም ጌታን ፈሩ፥ በጌታና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።


ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።


ሙሴም እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በዐይኖቻችሁ ፊት በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን፥ በአገልጋዮቹ ሁሉና በመላ አገሩ ላይ ያደረገውን አይታችኋል።


ስለዚህ እንደ ተቀመጣችሁበትም ዘመን መጠን፥ በቃዴስ ብዙ ቀን ተቀመጣችሁ።”


አርባ ዓመትስ የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?


የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios