ዘፀአት 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አቋራጭ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር በፍልስጥኤም ምድር በሚያልፈው መንገድ አልመራቸውም፤ “ጦርነት ቢያጋጥማቸው ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ ይመለሱ ይሆናል” ብሏልና። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እንዲህም ሆነ፤ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፥ “ሕዝቡ ሰልፉን በአየ ጊዜ እንዳይጸጽተው፥ ወደ ግብፅም እንዳይመለስ” ብሎአልና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እንዲህም ሆነ፤ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፥ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ” ብሎአልና። Ver Capítulo |