1 ዜና መዋዕል 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንበረም ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ።
የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በጌታም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደውን እሳት አቀረቡ።
ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እጅግ የተቀደሰ ነውና ለጌታ ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የተረፈውን የእህሉን ቁርባን ውሰዱ፥ እርሾም ያልገባበት ቂጣ አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤
ሙሴም የኃጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነው ፍየል አጥብቆ ጠየቀ፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ ብሎ ተቆጣ፦