መዝሙር 46:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፤ እግዚአብሔር በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑና የእግዚአብሔርን ሥራ፣ ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኑ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ፤ በምድር ላይ ያመጣውን ጥፋት ተመልከቱ። |
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ይህ ሰው እስከ መቼ እንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ፤ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን?” አሉት።
ፈርዖንም፥ ሹሞቹም ሁሉ፥ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ያጠፋታል፤ ባድማም ያደርጋታል፤ ይገለብጣትማል፤ በእርስዋም የተቀመጡትን ይበትናል።
ከጥንት ጀምሮ የፈረሱትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ያድሳሉ።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እኛ እናጠፋቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጊዜአቸው አልፎባቸዋል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው” ብለው ተናገሩአቸው።
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
“ጠላቶችህን ለመውጋት በወጣህ ጊዜ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን ሕዝቡንም ከአንተ ይልቅ በዝተው ባየህ ጊዜ፥ ከግብፅ ሀገር ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ፥ ያጠፉአቸው ዘንድ እንዳይራሩላቸው ፈጽመው እንዲያጠፉአቸው፥ ከእስራኤል ጋር ይጋጠሙ ዘንድ ልባቸውን እንዲያደነድኑ እግዚአብሔር ልባቸውን አጸና።