የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም።
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥ ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
አሁን ግን ጣልከን፤ አዋረድከንም፤ ከሚዘምተው ሠራዊታችን ጋር አብረህ መውጣትን ትተሃል።
ባለ ዕዳም ገንዘቡን ሁሉ ይበርብረው፥ የደከመበትንም ሁሉ ባዕድ ይበዝብዘው።
እጅህ ጠላትን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ።
አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤ ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
የዙፋንህ መሠረት ፍትሕና ርትዕ ነው፤ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።