ምሳሌ 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊቷም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንን ወጣት ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፤ ያለ ኀፍረት እንዲህ አለችው፦ |
ጌታ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ ስለዚህም አላፈርሁም፤ ፊቴንም እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፤ እንዳላፍርም አውቃለሁ።
ለአመንዝራዎች ሁሉ ዋጋ ይሰጡአቸዋል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር በዙሪያሽ ይገቡብሽ ዘንድ መማለጃን ትሰጫቸዋለሽ።
እነርሱ ፊታቸው የከፋ፥ ልባቸው የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው።
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥ፥ አትፍራቸው፤ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
እነርሱ በበለዓም ምክር በፌጎር ምክንያት የእስራኤልን ልጆች የሚያስቱ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዲስቱ የሚያደርጉ ዕንቅፋቶች ናቸውና፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆኖአል፤
ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤