Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 50:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳኝ፤ ስለ​ዚ​ህም አላ​ፈ​ር​ሁም፤ ፊቴ​ንም እንደ ባል​ጩት ድን​ጋይ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ፍ​ርም አው​ቃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና አልታወክሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ ኀፍረት ላይ እንደማልወድቅም አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልተዋረድኩም፤ ራሴን እንደ ጠንካራ ድንጋይ አበረታሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና ስለዚህ አልታወክሁም፥ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ እንዳላፍርም አውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 50:7
21 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና።


ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።


የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና።


ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፤ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኀጢአትን ትቶአልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ዕለት ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ድኅ​ነት በሚ​ደ​ረ​ግ​በ​ትም ቀን ረድ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ቃል ኪዳን አድ​ርጌ ለሕ​ዝቡ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆ​ኑ​ትን ርስ​ቶች ትወ​ርስ ዘንድ፤


እነሆ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፤ ማን ይጎ​ዳ​ኛል? እነሆ፥ ሁላ​ችሁ እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ላ​ችሁ፤ ብልም ይበ​ላ​ች​ኋል።


እነሆ በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በአ​ለ​ቆ​ች​ዋና በካ​ህ​ናቷ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመ​ሸ​ገች ከተማ፥ እንደ ብረ​ትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ብ​ር​ሃም ስለ ለየው ስለ ያዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ ይላል፥ “ያዕ​ቆብ አሁን አታ​ፍ​ርም፤ ፊት​ህም አሁን አይ​ለ​ወ​ጥም።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”


አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።


እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።


በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክን​ፍን ማን በሰ​ጠኝ አልሁ፥


ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios