እግዚአብሔርም ንጉሡን በደዌ ዳሰሰው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ለምጻም ሆነ፤ በተለየ ቤትም ይቀመጥ ነበር፤ የንጉሡም ልጅ ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሠልጥኖ ለሀገሩ ሕዝብ ይፈርድ ነበር።
ዘኍል 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራቁን በፊቷ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመለስ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ላይ ቢተፋባት እንኳ ኀፍረትዋን ተሸክማ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ትቈይ የለምን? ስለዚህም እርስዋ ከሰፈር ወጥታ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በገለልተኛ ቦታ ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሳ ወደ ሰፈር ልትገባ ትችላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰፈር ውጭ ተዘግታ ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ አለው። |
እግዚአብሔርም ንጉሡን በደዌ ዳሰሰው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ለምጻም ሆነ፤ በተለየ ቤትም ይቀመጥ ነበር፤ የንጉሡም ልጅ ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሠልጥኖ ለሀገሩ ሕዝብ ይፈርድ ነበር።
ቋቍቻውም በሥጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጕሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፤ በውኃም ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?