Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ቋቍ​ቻ​ውም በሥ​ጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆ​ዳ​ውም የጠ​ለቀ ባይ​መ​ስል፥ ጠጕ​ሩም ባይ​ነጣ፥ ካህኑ የታ​መ​መ​ውን ሰው ሰባት ቀን ይዘ​ጋ​በ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በቈዳው ላይ ያለው ቋቍቻ ነጭ ሆኖ ቢታይ፣ ነገር ግን ከቈዳው በታች ዘልቆ ባይገባና በቦታው ላይ የሚገኘው ጠጕር ወደ ነጭነት ባይለወጥ፣ ካህኑ በሽተኛውን ሰባት ቀን ያግልለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ቋቁቻው በሰውነቱ ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ በእርሱም ላይ ያለው ጠጉር ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን ቊስሉ ነጭ ሆኖ በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጐድ ብሎ ባይገኝና ጠጒሩም ወደ ነጭነት ባይለወጥ፥ ካህኑ ያን ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ቍቁቻውም በሥጋው ቁርበት ላይ ቢነጣ፥ ከቁርበቱም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጉሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 13:4
14 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሳቱ ጊዜ ጣዖ​ታ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋ​ው​ያን ሳይ​ቀር ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።


እርሱ በሥ​ጋው ቆዳ ላይ አሮጌ ለምጽ ነው፤ ካህ​ኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ እርሱ ርኩስ ነውና ይለ​የ​ዋል።


ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በቋ​ቁ​ቻው ጠጕሩ ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቆዳ​ውም ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥ ለምጽ ነው፤ ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ወጥ​ቶ​አል፤ ካህ​ኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና።


ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ በቋ​ቍ​ቻ​ውም ነጭ ጠጕር ባይ​ኖር፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


ካህ​ኑም በሥ​ጋው ቆዳ ያለ​ች​ውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕ​ሯም ተለ​ውጣ ብት​ነጣ በሥ​ጋው ቆዳ ያለች የዚ​ያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌ​ውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠ​ልቅ፥ እር​ስዋ የለ​ምጽ ደዌ ናት፤ ካህ​ኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበ​ለው።


ካህ​ኑም የቈ​ረ​ቈ​ሩን ደዌ ቢያይ፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ጥቁ​ርም ጠጕር ባይ​ኖ​ር​በት፥ ካህኑ የቈ​ረ​ቈር ደዌ ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ካህኑ ያችን ደዌ ይያት፤ እነ​ሆም፥ ያች ደዌ በፊት እንደ ነበ​ረች ብት​ሆን፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባት​ሰፋ፥ ካህኑ ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።


ካህ​ኑም ደዌ​ውን አይቶ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘ​ጋ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “አባቷ ምራ​ቁን በፊቷ ቢተ​ፋ​ባት ስንኳ ሰባት ቀን ታፍር ዘንድ ይገ​ባት ነበር፤ ሰባት ቀን ከሰ​ፈር ውጭ ተዘ​ግታ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ትመ​ለስ” አለው።


ማር​ያ​ምም ከሰ​ፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለ​ይታ ተቀ​መ​ጠች፤ ማር​ያ​ምም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ሕዝቡ አል​ተ​ጓ​ዙም።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ትፈ​ል​ጋ​ለህ ትመ​ረ​ም​ራ​ለ​ህም፤ ትጠ​ይ​ቃ​ለ​ህም፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ እንደ ተደ​ረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥


የአንዳንዶች ሰዎች ኀጢአት የተገለጠ ነው፤ ፍርድንም ያመለክታል፤ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos