እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
ሚክያስ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባዶ ቃላትን በመደርደር ስለ ወይንና ስለ ጠንካራ መጠጥ አስተምራችኋለሁ ቢላችሁ የዚህ ሕዝብ ነቢይ የሚሆነው እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል። |
እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰበሰበ፤ የእስራኤል ንጉሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፥ “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውም፤ የሐሰቱን ራእይ፥ ምዋርትንም፥ ከንቱንም ነገር፥ በልባቸውም የፈጠሩትን ይተነብዩላችኋል።”
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፥ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም” ይላሉ።
እነሆ ሐሰትን በሚያልሙ፥ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እኔም አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውምም፤ ለእነዚህ ሕዝብ በማናቸውም አይረቡአቸውም፥” ይላል እግዚአብሔር።
ነቢዩም ኤርምያስ ሐሰተኛውን ሐናንያን፥ “ሐናንያ ሆይ ስማ፤ እግዚአብሔር አልላከህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ኖን። ነቢያትሽ ከንቱና ዕብደትን አይተውልሻል፤ ምርኮሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።
እኔም ያልመለስሁትን የጻድቁን ልብ ወደ ዐመፃ መልሳችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኀጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።
ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።