La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የቍ​ር​ባ​ኑም መሥ​ዋ​ዕት የስ​እ​ለት ወይም የፈ​ቃድ ቢሆን፥ መሥ​ዋ​ዕቱ በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን ይብ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም የቀ​ረ​ውን በነ​ጋው ይብ​ሉት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱም ይበላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቁርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱም የቀረውን በማግስቱ ይበላ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አንድ ሰው የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ስእለት ስለ ተፈጸመለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ቢሆን ሁሉም በዚያው በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ ከዚያም የተረፈ ቢኖር በማግስቱ ይበላ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የቁርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱ በሚቀርብበት ቀን ይብሉት፤ ከእርሱም የቀረውን በነጋው ይብሉት፤

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 7:16
17 Referencias Cruzadas  

ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።


“የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤ ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ።


አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።


በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።


የም​ስ​ጋ​ና​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስት​ሠዉ እን​ዲ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ሠዉ​ለት።


እነ​ዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ታት ሌላ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ት​ሰ​ጡት ከስ​ጦ​ታ​ችሁ ሌላ፥ ከስ​እ​ለ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ከም​ታ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ቢሆን በበ​ዓ​ላ​ች​ሁም ቢሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእ​ለ​ቱን አብ​ዝ​ታ​ችሁ በአ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይን ጠጅ​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ዐሥ​ራት፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት፥ የተ​ሳ​ል​ኸ​ው​ንም ስእ​ለት ሁሉ፥ በፈ​ቃ​ድህ ያቀ​ረ​ብ​ኸ​ውን፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ መብ​ላት አት​ች​ልም።


ነገር ግን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገ​ር​ህን፥ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይዘህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ በዚያ እን​ዲ​ጠራ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ሂድ።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።