ዘሌዋውያን 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተቈረጠ ቢሆን፥ ቈጥረህ የራስህ ገንዘብ አድርገው እንጂ ለስእለት አይቀበልህም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 አካሉ ከመጠን በላይ የረዘመን ወይም ያጠረን በሬ ወይም በግ የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ይሁን እንጂ ስእለት ለመፈጸም ተቀባይነት አይኖረውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 የበሬው ወይም የበጉ የአካሉ ክፍል ረጅም ወይም አጭር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 አካሉ የጐደለ ወይም ቅርጹ የተበላሸ እንስሳ የበጎ ፈቃድ መሥዋዕት ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፤ ነገር ግን ስእለት የተፈጸመለት ሰው መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በሬው ወይም በጉ የተጨመረበት ወይም የጐደለበት ነገር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም። Ver Capítulo |