ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
ዘሌዋውያን 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሠራቸው ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና ሥርዐቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እነዚህን የሚጠብቅ ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናልና፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፥ እነርሱን የሚያደርግ ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የምሰጣችሁን ኅጎቼንና ሥርዓቴን ጠብቁ፤ ይህን በማድረግ ማናቸውም ሰው ሕይወቱን ያድናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚሠራቸው ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
እግዚአብሔር ሙሴን፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር” ብሎ ተናገረው።
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን የእስራኤልን ቤት በምድረ በዳ በትእዛዜ ሂዱ አልኋቸው፤ አልሄዱምም፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ሕጌን አፈረሱ፤ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ልጆቻቸው ግን አማረሩኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጉትም፤ በሥርዐቴም አልሄዱም፤ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።
“ከእናንተም ማንም ሰው ኀፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ፥ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥናውም።”
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።