Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ኦሪ​ትስ ሠርቶ የፈ​ጸመ ይኖ​ር​በ​ታል እንጂ በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ ነገር ግን “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናል” ተብሏል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሕግ ከእምነት አይደለም፤ ነገር ግን “የሚፈጽማቸው በእነርሱ ይኖራል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ እንዲያውም “ሰው በሕግ ሊኖር የሚችለው የሕግ ትእዛዞችን ሁሉ ሲፈጽም ነው” ተብሎ ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን፦ የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 3:12
13 Referencias Cruzadas  

የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም።


የኦ​ሪ​ትን ሕግ የፈ​ጸመ ብቻ ተስፋ የሚ​ያ​ገኝ፥ ዓለ​ም​ንም የሚ​ወ​ርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአ​ብ​ር​ሃም እም​ነቱ ባል​ጠ​ቀ​መ​ውም ነበር፤ ተስ​ፋ​ው​ንም ባላ​ገ​ኘም ነበር።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ።


ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


በጸጋ ከጸ​ደቁ ግን በሥ​ራ​ቸው አይ​ደ​ለማ፤ በሥ​ራም የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ ጸጋ ጸጋ አይ​ባ​ልም።


እርሱም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ፤” አለው።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios