Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሙሴ በሕግ በኩል የሆነውን ጽድቅ ሲገልጽ፣ “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናል” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሙሴ በሕግ ስለ ሆነው ጽድቅ ሲጽፍ “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ይኖራል” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሕግን በመከተል ስለሚገኘው ጽድቅ ሙሴ የጻፈው “ሕግን የሚፈጽም ሁሉ በሕይወት ይኖራል” የሚል ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 10:5
11 Referencias Cruzadas  

ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት።


ኦሪ​ትስ ሠርቶ የፈ​ጸመ ይኖ​ር​በ​ታል እንጂ በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ አይ​ደ​ለም።


“አሁ​ንም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ርሱ፥ ዛሬ የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos