Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለሕ​ይ​ወት የተ​ሠ​ራ​ች​ልኝ ያቺ ሕግ ለሞት ሆና አገ​ኘ​ኋት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ለሕይወት እንዲሆን የታሰበው ያ ትእዛዝም ሞትን እንዳመጣ ተገነዘብሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እኔም ሞትሁ፤ ለሕይወትም የተሰጠው ትእዛዝ ለሞት መሆኑን ተገነዘብሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለሕይወትም የተሰጠው የሕግ ትእዛዝ በእኔ ላይ ሞትን አመጣብኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 7:10
10 Referencias Cruzadas  

ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ሙሴም “የኦ​ሪ​ትን ጽድቅ መሥ​ራ​ትን የፈ​ጸመ ሁሉ በእ​ርሱ ይጸ​ድ​ቅ​በ​ታል” አለ።


የኦ​ሪት ሕግ በአ​ፍ​ራሹ ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣ​ልና፤ የኦ​ሪት ሕግም ከሌለ መተ​ላ​ለፍ የለም።


እኔም ቀድሞ ኦሪት ሳት​ሠራ ሕያው ነበ​ርሁ፤ የኦ​ሪት ትእ​ዛዝ በመ​ጣች ጊዜ ግን ኀጢ​አት ሕይ​ወ​ትን አገ​ኘች፤ እኔ ግን ሞትሁ።


ስለ​ዚያ ስለ አለ​ፈው የፊቱ ብር​ሃን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሙ​ሴን ፊት መመ​ል​ከት እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ በዚ​ያች በድ​ን​ጋይ ላይ በፊ​ደል ለተ​ቀ​ረ​ጸች ለሞት መል​እ​ክት ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት፥


ኦሪ​ትስ ሠርቶ የፈ​ጸመ ይኖ​ር​በ​ታል እንጂ በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ አይ​ደ​ለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos