La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት ሕዝብ አል​ዓ​ዛ​ርን ከመ​ቃ​ብር እንደ ጠራው፥ ከሙ​ታ​ንም እንደ አስ​ነ​ሣው መሰ​ከ​ሩ​ለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ባስነሣበት ጊዜ፣ ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መነሣቱን ይመሰክሩ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ አብረውት የነበሩ ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይመሰክሩ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 12:17
17 Referencias Cruzadas  

አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


ዮሐ​ን​ስም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ከሰ​ማይ እንደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀ​መጥ አየሁ።


እኔም ራሴ አይ​ቻ​ለሁ፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።”


ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አት መጥ​ተው በቤት ከእ​ር​ስዋ ጋር የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም ፈጥና ተነ​ሥታ እንደ ወጣች ባዩ ጊዜ በዚያ ለወ​ን​ድ​ምዋ ልታ​ለ​ቅስ ወደ መቃ​ብሩ የም​ት​ሄድ መስ​ሎ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አት።


እኔም ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ማኝ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ቆመው ስላ​ሉት ሰዎች ይህን እና​ገ​ራ​ለሁ።”


ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ።


ያየ​ውም መሰ​ከረ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት ነው፤ እር​ሱም እና​ንተ ልታ​ምኑ እው​ነት እን​ደ​ሚ​ና​ገር ያው​ቃል።


ስለ​ዚህ ነገር ምስ​ክር የሆነ፥ ስለ እር​ሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝ​ሙር ነው፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእኛ መካ​ከል በገ​ባ​በ​ትና በወ​ጣ​በት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብ​ረው ከነ​በ​ሩት ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የት​ን​ሣ​ኤዉ ምስ​ክር ይሆን ዘንድ ይገ​ባል።”


እኛም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮቹ ነን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ዘ​ዙት የሰ​ጣ​ቸው መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክር ነው።”


እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።