Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 12:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ አብረውት የነበሩ ሁሉ ስለ ኢየሱስ ይመሰክሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ባስነሣበት ጊዜ፣ ከርሱ ጋራ የነበሩ ሰዎች መነሣቱን ይመሰክሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከዚ​ያም አብ​ረ​ውት የነ​በ​ሩት ሕዝብ አል​ዓ​ዛ​ርን ከመ​ቃ​ብር እንደ ጠራው፥ ከሙ​ታ​ንም እንደ አስ​ነ​ሣው መሰ​ከ​ሩ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 12:17
17 Referencias Cruzadas  

ዮሐንስም ስለ እግዚአብሔር ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አስተማረው እውነት፥ እንዲሁም ስላየውም ነገር ሁሉ መሰከረ።


ስለዚህ ነገር እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ የሰጣቸው መንፈስ ቅዱስም ምስክር ነው።”


እንዲሁም ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ አብረውን ከነበሩት ከነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”


ይህን ያየ፥ እናንተ እንድታምኑ መሰከረ፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ የሚናገረውም እውነት እንደ ሆነ፥ እርሱ ያውቃል።


በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።


ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ የመሰከረና እነዚህንም ነገሮች የጻፈ ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ የእርሱም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።


ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያልኩት፥ እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምኑ ብዬ ነው” አለ።


እርስዋን ለማጽናናት መጥተው በቤት ውስጥ አብረዋት የነበሩ አይሁድ ማርያም በፍጥነት ተነሥታ ስትወጣ አይተው ወደ አልዓዛር መቃብር ሄዳ የምታለቅስ መስሎአቸው ተከተሉአት።


እኔም ይህን አይቼአለሁ፤ ስለዚህ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እመሰክራለሁ።”


ቀጥሎም ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ከሰማይ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍበት አየሁ፤


የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios