ዮሐንስ 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከአይሁድም ብዙ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ በዚያ እንዳለ በዐወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመጡትም ጌታችን ኢየሱስን ለማየት ብቻ አልነበረም፤ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ለይቶ ያስነሣዉን አልዓዛርንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁድ ኢየሱስ በዚያ መኖሩን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ብለው ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ከአይሁድም ብዙ ሰዎች በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፤ የመጡትም በኢየሱስ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ከአይሁድም ብዙ ሕዝብ በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፥ ከሙታንም ያስነሣውን አልዓዛርን ደግሞ እንዲያዩ ነበረ እንጂ ስለ ኢየሱስ ብቻ አይደለም። Ver Capítulo |