ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
ኤርምያስ 51:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥፋት በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ተዋጊዎችዋ ተያዙ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ተበቅሎአቸዋልና፥ እግዚአብሔርም ፍዳን ከፍሎአቸዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣል፤ ጦረኞቿ ይማረካሉ፤ ቀስታቸውም ይሰበራል፤ እግዚአብሔር ግፍን የሚበቀል፣ ተገቢውንም ሁሉ የሚከፍል አምላክ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አጥፊዎች በባቢሎን ላይ ስለ ዘመቱ ወታደሮችዋ ተማረኩ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እኔ ለሁሉም እንደየሥራው ዋጋውን የምከፍል አምላክ ስለ ሆንኩ፥ ባቢሎን በፈጸመችው ግፍ መጠን ፍዳዋን እከፍላታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፥ እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል። |
ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
ከባድ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው ይወነጅላል፤ በደለኛውም ይበድላል። የኤላም ሰዎችና የሜዶን መልእክተኛ በእኔ ላይ ይመጣሉ። ዛሬ ግን እጨነቃለሁ፤ እረጋጋለሁም።
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ዋና የኀይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።
በጽዮን በዐይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እበቀላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር፥ በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን ደስ ይላቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።
በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፤ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ አላባሽ አግሬ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።
“የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና፥ አንተ እንደ አደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፤ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።
የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።