እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት።”
ኤርምያስ 49:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሀትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፤ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣ ሽብር አመጣብሻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤ በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ በአንቺ ላይ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከሁሉም አቅጣጫ ሽብር አመጣባችኋለሁ፤ ሁላችሁም ትሸሻላችሁ፤ ሁሉም ወደፊቱ ሸሽቶ ስለሚበታተን የሸሹትን ስደተኞች የሚሰበስብ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። |
እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት።”
አርኖንም በምትኖርበት ምሽግ መጠለያን ትሠራ ዘንድ ብዙ ትመክራለች፤ በቀትር ጊዜ እንደ ሌሊት ደንግጠው ይሸሻሉ፤ ወደ እናንተም አታስገቡአቸው።
መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተዋል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጭንቀትንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ አንተን ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር አፈልስሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤ ዐይኖችህም ያያሉ፤ አንተንና ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኀያላኖቻቸውም ሲደክሙ፥ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙሪያቸውም ይከቡአቸዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ድንኳናቸውንና በጎቻቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ፥ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፤ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።
ሳምኬት። እናንተ ከርኩሳን ራቁ፥ አስተምሩአቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉአቸው፤ አትንኩአቸውም። ታውከዋልና ዳግመኛ እንዳይኖሩባት ለአሕዛብ ንገሩአቸው።
“ዕራቁታችሁን ያወጡአችኋል፤ እርስ በርሳችሁም ትተያያላችሁ፤ በሬማንም ተራራ ትጣላላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደ ሰጣችሁ ዐወቅሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን መፍራትን በላያችን አምጥትዋልና፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ የተነሣ ቀልጠዋልና።