ከለዳውያንንም ፈርተው ነበርና ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ፥ የሠራዊቱም አለቆች ተነሥተው ወደ ግብፅ ገቡ።
ኤርምያስ 43:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰሙምና ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍናስ ድረስም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርንም ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብጽ ገቡ፤ ዘልቀውም እስከ ጣፍናስ ድረስ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታንም ድምፅ አልሰሙምና ወደ ግብጽ ምድር ገቡ፥ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ወደ ግብጽ ሄደው እስከ ጣፍናስ ከተማ ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰሙምና ወደ ግብጽ ምድር ገቡ፥ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ። |
ከለዳውያንንም ፈርተው ነበርና ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ፥ የሠራዊቱም አለቆች ተነሥተው ወደ ግብፅ ገቡ።
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ፥ በሜምፎስም፥ በፋቱራም ሀገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፥ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
የግብፅን ቀንበር በዚያ በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይጠፋባታል፤ ደመናም ይጋርዳታል፤ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ።