La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 35:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ፣ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦

Ver Capítulo



ኤርምያስ 35:1
14 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖን ኒካ​ዑም የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወ​ጠው። ዮአ​ክ​ስ​ንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈ​ለ​ሰው፤ በዚ​ያም ሞተ።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም ብሩ​ንና ወር​ቁን ለፈ​ር​ዖን ሰጠው፤ እንደ ፈር​ዖ​ንም ትእ​ዛዝ ገን​ዘብ ይሰጥ ዘንድ ምድ​ሩን አስ​ገ​በረ፤ ለፈ​ር​ዖን ኒካ​ዑም ግብር ይሰጥ ዘንድ ከሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ እንደ ግም​ጋ​ሜው ብርና ወርቅ አስ​ከ​ፈለ።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጣ፤ አለም፦


“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አለ​ቆች ሁሉ ማርኮ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ባፈ​ለ​ሳ​ቸው ጊዜ፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ኢዮ​አ​ቄ​ምን እን​ዲህ በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በር​ግጥ ይመ​ጣል፤ ይች​ንም ሀገር ያፈ​ር​ሳ​ታል፤ ሰውና እን​ስ​ሳም ያል​ቃሉ ብለህ ለምን ጻፍ​ህ​በት? ብለህ ይህን ክር​ታስ አቃ​ጥ​ለ​ሃል።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​አ​ቄም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መጡ ሕዝብ ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ጾም ዐዋጅ ነገሩ።


በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥