ኤርምያስ 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰውነቴ ጕድጓድን ቈፍረዋል፤ በውኑ በመልካም ፈንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ፥ ቍጣህንም ከእነርሱ ትመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ ቍጣህንም ከእነርሱ እመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ። |
እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል።
አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ በመከራቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱ አትጸልይ፤ በምልጃና በጸሎት አትማልድ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው።
እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ።”
እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ስለዚህ ሕዝብ አንተ አትጸልይ፤ ይቅር እላቸው ዘንድ አትማልደኝ፤ የእነርሱን ነገር አልሰማህምና ትለምንላቸው ዘንድ ወደ እኔ አትምጣ።”
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ በየትኛው ሥራ ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?”
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካም ተናገረ እንዲህም አለው፥ “እርሱ አልበደለህምና፥ ሥራውም ለአንተ እጅግ መልካም ሆኖአልና ንጉሡ ባሪያውን ዳዊትን አይበድለው፤