La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ሙታን ሕይ​ወ​ትን አያ​ዩ​አ​ትም፤ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶ​ችም አያ​ስ​ነ​ሡም፤ ስለ​ዚ​ህም አንተ አም​ጥ​ተ​ሃ​ቸ​ዋል፤ አጥ​ፍ​ተ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱ ሞተዋል፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም፤ መንፈሳቸው ተነሥቶ አይመጣም። አንተ ቀጣሃቸው፤ አጠፋሃቸው፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ደመሰስህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤ አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥ ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፥ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፥ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል አጥፍተሃቸውማል፥ መታሰቢያቸውንም ሁሉ ምን ምን አድርገሃል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 26:14
25 Referencias Cruzadas  

መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም ከም​ድር ይጠ​ፋል፤ በም​ድ​ርም ስም አይ​ቀ​ር​ለ​ትም።


ከዚ​ህም በኋላ ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ባል። እንደ ጤዛ ትነት ይጠ​ፋል። እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፈ​ለ​ዋል። ዐመ​ፀ​ኛም ሁሉ እንደ በሰ​በሰ ዛፍ ይሰ​በ​ራል።


ደመና ከሰ​ማይ ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ፥ እን​ዲሁ ወደ መቃ​ብር የሚ​ወ​ርድ ሰው ዳግ​መኛ አይ​ወ​ጣም።


በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።


ታላ​ላቅ ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ኀጢ​አ​ተኛ ጻድ​ቁን ይመ​ለ​ካ​ከ​ተ​ዋል፥ ጥር​ሱ​ንም በእ​ርሱ ላይ ያፋ​ጫል።


ወዳ​ጆ​ች​ህም፥ እን​ዲ​ድኑ በቀ​ኝህ አድን፥ ስማ​ኝም።


ጠላ​ቶች በጦር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠፉ፥ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረ​ስህ፥ ዝክ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ን​ድ​ነት ታጠ​ፋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅ አዳ​ና​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሞቱ በባ​ሕር ዳር አዩ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ሕያ​ዋን እን​ዲ​ሞቱ ያው​ቃ​ሉና፤ ሙታን ግን አን​ዳች አያ​ው​ቁም፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውም ተረ​ስ​ቶ​አ​ልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላ​ቸ​ውም።


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


ድን​ገ​ትም ፈጥኖ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ጐ​ድ​ጓድ፥ በም​ድ​ርም መና​ወጥ፥ በታ​ላቅ ድምፅ፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በወ​ጨ​ፎም፥ በም​ት​በ​ላም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይጐ​በ​ኛ​ታል።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


“የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ” አለ።


በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።


የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው።