ኢሳይያስ 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርና የቍጣው ሠራዊት ዓለምን ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ ሀገር ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ ከሩቅ አገር፣ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታና የቁጣው ጦር መሣሪያ፤ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፤ ከሩቅ አገር፤ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በምድር ዳርቻ ከሚገኙ ከሩቅ አገሮች የመጡ ናቸው፤ እግዚአብሔር አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት የቊጣ መሣሪያ የሆነ ሠራዊቱን አሰልፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርና የቍጣው የጦር ዕቃ ምድርን ሁሉ ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ አገር ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ። |
እነሆ፥ እግዚአብሔር ዓለምን ያጠፋታል፤ ባድማም ያደርጋታል፤ ይገለብጣትማል፤ በእርስዋም የተቀመጡትን ይበትናል።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ ቍጣውም ከከንፈሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነድዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተመላ ነው፤ የቍጣውም መቅሠፍት እንደምትበላ እሳት ናት፤
የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ነውና፤ መቅሠፍቱም ያጠፋቸውና ለጦር ይሰጣቸው ዘንድ በቍጥራቸው ልክ ነው።
ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ይሰማሉ፤ ይህን ማን ነገራቸው? አንተን በመውደድ የከለዳውያንን ዘር አስወግድ ዘንድ ፈቃድህን በባቢሎን ላይ አደረግሁ።
በሩቅ ላሉ አሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።
ታያላችሁ፤ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፤ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፤ ዐላውያንንም ያጠፋቸዋል።”
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝንብ፥ በአሦርም ሀገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለውና እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል።
ሕዝቤ ከሰሜን በእርስዋ ላይ ወጥትዋል፤ ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
እነሆ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አነሣለሁ፤ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ፤ ከዚያም ትወሰዳለች፤ ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
እነሆ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተቀረፁ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድን ነው?
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”