Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 50:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሰሜን አንድ መንግሥት መጥቶ ይወጋታል፤ ምድሯንም ባድማ ያደርጋል፤ የሚኖርባትም አይገኝም፤ ሰዎችና እንስሳትም ሸሽተው ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሕዝብ ከሰሜን በእርሷ ላይ ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በባቢሎን ላይ አደጋ ጥሎ ምድረ በዳ የሚያደርጋት ሕዝብ ከሰሜን በኩል ተነሥቶባታል፤ ሰውም እንስሳውም ጥሎአት ይሸሻል፤ የሚኖርባትም የለም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:3
22 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን ሰው ከም​ድር ላይ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ከሰው እስከ እን​ስ​ሳና አራ​ዊት፥ እስከ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠ​ር​ኋ​ቸው ተጸ​ጽ​ቻ​ለ​ሁና” አለ።


እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦


በዚ​ህ​ችም ከተማ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን እመ​ታ​ለሁ፤ በጽ​ኑም ቸነ​ፈር ይሞ​ታሉ።


እነሆ ከሰ​ሜን ምድር የታ​ላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን ጉባኤ አነ​ሣ​ለሁ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ይሰ​ለ​ፋሉ፤ ከዚ​ያም ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ባዶ​ውን እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ እንደ ብልህ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


አጥ​ፊ​ዎች ከሰ​ሜን ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ሰማ​ይና ምድር፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢ​ሎን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል።


እን​ግ​ዲህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣ​ዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎ​ችና በም​ድር ፍሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።”


በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፣ የሰማይን ወፎችና የባሕርን ዓሣዎች ማሰናከያንም ከኃጢአተኞች ጋር አጠፋለሁ፣ ሰውንም ከምድር ፊት እቈርጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos