La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም ወደ እነ​ርሱ ሳይ​ቀ​ርብ ከሩቅ አስ​ቀ​ድ​መው አዩት፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ በእ​ርሱ ላይ ተማ​ከሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ አዩት፤ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም በሩቅ አዩት፤ ወደ እነርሱም ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱ በሩቅ ሳለ አዩት ወድ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:18
19 Referencias Cruzadas  

ዔሳ​ውም አባቱ ስለ ባረ​ከው በያ​ዕ​ቆብ ቂም ያዘ​በት፤ ዔሳ​ውም በልቡ አለ፥ “ለአ​ባቴ የል​ቅሶ ቀን ትቅ​ረብ፤ ወን​ድ​ሜን ያዕ​ቆ​ብን እገ​ድ​ለ​ዋ​ለሁ።”


አን​ዱም ለአ​ንዱ እን​ዲህ አለው፥ “ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ።


የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች አባ​ታ​ቸው እንደ ሞተ በአዩ ጊዜ እን​ዲህ አሉ፥ “ምና​ል​ባት ዮሴፍ ያደ​ረ​ግ​ን​በ​ትን ክፋት ያስ​ብ​ብን ይሆ​ናል፤ ባደ​ረ​ግ​ን​በ​ትም ክፋት ሁሉ ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ብን ይሆ​ናል።”


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙም።


እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም።


ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥ መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥ ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።


ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤


እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለው፤ ርስቱም ለኛ ይሆናል፤’ ተባባሉ።


ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።


ከዚ​ያ​ችም ቀን ጀምሮ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ሊገ​ድ​ሉት ተማ​ከሩ።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


ሳኦ​ልም ለልጁ ለዮ​ና​ታ​ንና ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ዳዊ​ትን ይገ​ድሉ ዘንድ ነገ​ራ​ቸው። የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ግን ዳዊ​ትን እጅግ ይወ​ድ​ደው ነበር።