ዘፍጥረት 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ባሕርና እስከ አዜብ እስከ መስዕና እስከ ምሥራቅ ይበዛል፤ ይሞላልም፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ፥ በዘርህም ይባረካሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። |
ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፥ “ዐይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ መስዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤
አንተም፦ ‘በርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።’ ”
ከከፉ ነገር ሁሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም፥ የአባቶች የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”
አባቱም እንቢ አለ፤ እንዲህ ሲል፥ “አውቃለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቃለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆናል።”
ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፤ ለዘለዓለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸው ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ዐስብ።”
እንደ ገናምበቀኝና በግራ ተስፋፊ፤ ዘርሽ አሕዛብን ይወርሳሉና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ታደርጊያለሽና።
የያዕቆብን ዘር ማን ያውቀዋል? የእስራኤልንስ ሕዝብ ማን ይቈጥረዋል? ሰውነቴም ከጻድቃን ሰውነት ጋር ትሙት፤ ዘሬም እንደ እነርሱ ዘር ትሁን።”
እናንተም የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እግዚአብሔር ለአባቶቻችን በሠራው ሥርዐትም የተወለዳችሁ ናችሁ፤ ለአብርሃም፦ ‘በዘርህ የምድር አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎታልና።
እግዚአብሔርም ለአብርሃም፥ “ለአንተና ለዘርህ” ብሎ ተስፋ ሰጠው፤ ለብዙዎች እንደሚናገር አድርጎ ለአንተና ለዘሮችህ አላለውም፤ ለአንድ እንደሚናገር አድርጎ፥ “ለዘርህ” አለው እንጂ ይኸውም ክርስቶስ ነው።
እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቃቸው መጽሐፍ አስቀድሞ ገልጦአልና፤ አሕዛብም ሁሉ በእርሱ እንዲባረኩ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአብርሃም ተስፋ ሰጠው።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
“አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ድንበርህን ባሰፋልህ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰውነትህ ከወደደችው ሁሉ ብላ።
የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ።
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤