La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 27:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፤ ተነ​ሣና በሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል ወደ ካራን ምድር ወደ ወን​ድሜ ወደ ላባ ሂድ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ልጄ ሆይ፤ እኔ የምልህን አድርግ፤ በካራን ምድር ወደሚኖረው ወደ ላባ ቶሎ ሽሽ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ፥ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁንም ልጄ ሆይ፥ የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚኖረው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 27:43
14 Referencias Cruzadas  

ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ለር​ብ​ቃም ስሙ ላባ የተ​ባለ ወን​ድም ነበ​ራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ ወደ ሰው​ዬው ሮጠ።


ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


እና​ቱም አለ​ችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መር​ገ​ምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያል​ሁ​ህን አም​ጣ​ልኝ።”


ለር​ብ​ቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነ​ገ​ራት፤ ታና​ሹን ልጅ​ዋን ያዕ​ቆ​ብ​ንም ልካ ጠራ​ችው፤ አለ​ች​ውም፥ “እነሆ ወን​ድ​ምህ ዔሳው ያድ​ድ​ን​ሃል፤ ሊገ​ድ​ል​ህም ይፈ​ል​ጋል።


አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ስማኝ፤


ያዕ​ቆ​ብም ከአ​ዘ​ቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።


ይስ​ሐ​ቅም ልጁ ያዕ​ቆ​ብን ላከው፤ እር​ሱም የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሚ​ሆን የሶ​ር​ያ​ዊው ባቱ​ኤል ልጅ ላባ ወዳ​ለ​በት ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሄደ።


ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባ​ቱ​ንና የእ​ና​ቱን ቃል ሰምቶ ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ሄደ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚ​ያም ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ምህ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸህ ጊዜ ለተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ለእኔ መሥ​ው​ያን ሥራ።”


የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ ልጆቹ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ይ​ጠጡ ያዘ​ዛ​ቸው ቃል ተፈ​ጸመ፤ ለአ​ባ​ታ​ቸ​ውም ትእ​ዛዝ ታዝ​ዘ​ዋ​ልና እስከ ዛሬ ድረስ ወይን አይ​ጠ​ጡም፤ እኔም በማ​ለዳ ስለ እና​ንተ ተና​ገ​ርሁ፤ ሆኖም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።


ጴጥ​ሮ​ስና ሐዋ​ር​ያ​ትም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ለሰው ከመ​ታ​ዘዝ ይልቅ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ ይገ​ባል።