እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ዘፍጥረት 24:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርብቃንም እንዲህ ብለው መረቋት፤ “እኅታችን ሆይ፤ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽ የጠላቶቹን ደጆች ይውረስ”። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርብቃንም መረቁአትና፦ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፥ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ” አሉአት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንቺ እኅታችን የብዙ ሺህ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዘሮችሽም የጠላቶቻቸውን ከተሞች ይውረሱ!” ብለው ርብቃን መረቁአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርብቃንም መረቁአትና፦ አንቺ እኅታችን እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ አሉአት። |
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ርብቃም ተነሣች፤ ደንገጥሮችዋም፥ በግመሎችዋ ላይ ተቀምጠው ከሰውዬው ጋር አብረው ሄዱ፤ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ።
ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።
በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “በእናንተ እስራኤል እንዲህ ተብሎ ይባረካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ይባርክህ።” ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ።
ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ታወርሱአቸዋላችሁ፤ እነርሱም ለእናንተ ለዘለዓለም ውርስ ይሆናሉ፤ ነገር ግን ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ማናቸውም ሰው ወንድሙን በሥራ አያስጨንቀው።