መክብብ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ። |
ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥
ለሰው ልጆች ሞት አለባቸው፥ ለእንስሳም ሞት አለባቸው፤ አንድ ሞት አለባቸው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ ለሁሉም አንድ እስትንፋስ አላቸው፥ ሰው ከእንስሳ ብልጫው ምንድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለውም።
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
የሰማይ መስኮቶችም ተከፍተዋልና፥ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሀት ድምፅ የሸሸ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።
ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆንባችኋል።
ሲሄዱም አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ።
ኤፍሬም ከእግዚአብሔር ጋር ጉበኛ ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመንገዱ ሁሉ ላይ ክፉ ወጥመድ ሆነ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ርኵሰትን አደረጉ።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለቤት ሌባ የሚመጣበትን ጊዜ ቢያውቅ ተግቶ በጠበቀ፥ ቤቱንም እንዲቈፍሩት ባልፈቀደም ነበር።
ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤