Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለዚህ የማይድን ውድቀትና መመታት፥ ጥፋትም ድንገት ይደርስበታል፤ እግዚአብሔር በሚጠላቸው ሁሉ ደስ ይለዋልና፤ ስለ ነፍሱ ርኵሰትም ይደቅቃልና፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ ጥፋት ድንገት ይደርስበታል፥ ድንገት ይደቅቃል፥ ፈውስም ከቶ የለውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህም በድንገት ጥፋት ይደርስበታል፤ ሊድን በማይችልበት ሁኔታ በቅጽበት ይወድማል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 6:15
15 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በሕ​ዝቡ ላይ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ፥ ፈው​ስም እስ​ከ​ማ​ይ​ገ​ኝ​ላ​ቸው ድረስ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክ​ተ​ኞች ይሳ​ለቁ፥ ቃሉ​ንም ያቃ​ልሉ፥ በነ​ቢ​ያ​ቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።


ስለዚህ እኔ በጥፋታችሁ እሥቃለሁ፤ ጥፋትም በመጣባችሁ ጊዜ ደስ ይለኛል።


እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ናቸው፥ ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤


ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። ኃጥኣን ግን በክፉ ደዌ ይያዛሉ።


እነርሱ ኀጢአተኞችን ድንገት ይበቀሏቸዋልና፤ የሁለቱንስ ፍርድ ማን ያውቃል?


ትን​ቢ​ትም በተ​ና​ገ​ርሁ ጊዜ የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥያ ሞተ፤ እኔም በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! ወዮ​ልኝ! በውኑ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኽሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios